ተመራቂዎች ዕውቀት፣ ጊዜ፣ ጉልበት እና ተሰጥኦን በማንኛውም ሁኔታና ወቅት በመጠቀም ህብረተሰቡን በንጽህና ምሳሌ በመሆን ማገልገል አለባችሁ – ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)

ተመራቂዎች ዕውቀት፣ ጊዜ፣ ጉልበት እና ተሰጥኦን በማንኛውም ሁኔታና ወቅት በመጠቀም ህብረተሰቡን በንጽህና ምሳሌ በመሆን ማገልገል አለባችሁ – ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)

ተመራቂዎች ዕውቀት፣ ጊዜ፣ ጉልበት እና ተሰጥኦን በማንኛውም ሁኔታና ወቅት በመጠቀም ህብረተሰቡን በንጽህና ምሳሌ በመሆን ማገልገል አለባችሁ ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪና ዲፕሎማ መርሃ ግብር ለ6ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 2 ሺ 1 መቶ 48 ተማሪዎችን አስመርቋል::

በምረቃ ፕሮግራሙ በክብር እንግድነት የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎች ጊዜ፣ ጉልበት እና ተሰጥኦን በማንኛውም ሁኔታና ወቅት በመጠቀም በንጽህና ምሳሌ በመሆን ህብረተሰቡን ማገልገል አለባችሁ ብለዋል።

ስኬታማ መሀንዲስ በመሆን ስኬታማ ህይወት ለመኖር መመረቅ ብቻውን በቂ ስለማይሆን ራሳችሁን በጥልቀት ማወቅ አለባችሁ ብለዋል።

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ከመንግስት ጎን በመቆም በትምህርቱ ዘርፍ የተማረ ኃይል ከማፍራቱም ባለፈ በማህበራዊና በልማታዊ ጉዳዮች በመሳተፍ ለዘላቂ ልማትና እድገት እየተጋ ያለ ኮሌጅ መሆኑንም አስረድተዋል።

ኮሌጁ የጀመራቸውን ሁለንተናዊ የትምህርት የምርምር ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል በማሳሰብ።

ሀገሪቱንና እና ክልሉን ከድህነትና ስራ አጥነት ችግር ለማላቀቅ ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ስራ ጠባቂ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ በመሆን ህብረተሰቡን እና ሃገርን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል አንዳለባቸውም ዶ/ር ዲላም ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ተሰማ አበራ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ኮሌጁ በ2010 ዓ.ም ተመስርቶ ተልእኮውን እውን ለማድረግ በጥናት ላይ የተመረኮዘ የአምስት ዓመት እስትራቴጂ ዕቅድ በማውጣት ዕውቅና ባገኘባቸው በተለያዩ ትምህርት መስኮች ከዲፕሎማ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ዜጎችን አሰልጥኖ እያስመረቀ ይገኛል።

በአሁኑ ጊዜም ኮሌጁ ከ4 መቶ በላይ ለሆኑ ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።

ኮሌጁ መማር እየፈለጉ የአቅም ችግር ለገጠማቸው ለ40 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እየሰጠ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ተሰማ፤ ከመማር ማስተማር ስራ ጎን ለጎን የተለያዩ ማህበራዊና ልማታዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ኮሌጁን በ2030 የምስራቅ አፍሪካ ታዋቂ የትምህርትና የምርምር ልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች በሰጡት ሀሳብ በኮሌጁ ቆይታ ባገኙት ከሥራ ፈላጊነት በመላቀቅ ሥራ ፈጣሪ በመሆን ሕዝብና ሀገርን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ኤልያስ ኤርሶ – ከሆሳዕና ጣቢያችን