የጋሞ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሐ ግብር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 23ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ
ሁሉም የምክር ቤት አባላት መገኘታቸውንና ምልዓተ ጉባኤው መሟላቱን ያረጋጡት የዞኑ ሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤዋ ወ/ት አለሚቱ ዮሴፍ፤ ጉባኤው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።
በዚህ ጉባኤ የዞኑ ሕዝብ ምክር ቤት፣ የዞኑ አስተዳደር ምክር ቤት እንዲሁም የከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጎ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የ2018 በጀት ዓመት እቅድና ረቂቅ በጀት እንዲሁም ሹመት ለምክር ቤቱ ቀርቦ እንደሚፀድቅ የወጣው መርሃ-ግብር ያመልክታል።
ዘጋቢ፡ አዕላፍ አዳሙ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ