የወላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ጤናዬ ትርንጎ በመክፈቻ ንግግራቸው የዞኑ ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ጠንካራ ሥራ ተሰርቶ የላቀ ውጤት መመዝገቡንም ጠቁመዋል።
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ብርቱ ጥረት እየተደረገ ያለ ቢሆንም ውስንነት እንዳለ በማንሳት፤ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከወረዳና ቀበሌ ምክር ቤቶች ጋር በመቀናጀት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ጉባኤው በ8 አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ የሚያስተላልፍ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የዕለት ደራሽ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ