‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ቃል የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ
የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አካላት እንደተናገሩት በዩኒቨርስቲው ግቢ እንደተቋም በሀገር ደረጃ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ለማሳካት የበኩላቸውን አሻራ ከማኖራቸው ባሻገር የተከሉት ችግኞች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡
በዩኒቨርስቲው የምርምርና ዓለም ዓቀፍዊ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ኩማንደር መሐመድ እንደተናገሩት እየተከናወነ ያለው የችግኝ ተከላ ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል ተከትሎ በደን መሳሳት ምክንያት ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ከወዲሁ ለመከላከል ታስቦ እንደሆነ ገልፀው እንደ ዩኒቨርስቲው በሁሉ አቀፍ ዘርፍ የበኩላቸውን ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የጂንካ ዩኒቨርስቲ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቅዱሱ ዬታ እንደ ሀገር የተቀመጠው እንሼቲቭ አካል የሆነው ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የክረምት ወራት አንዱ ተግባር በማድረግ በአንድ ጀምበር 4ሺህ5መቶ በላይ ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ሁሉንም የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በማሳተፍ ማሳካት መቻሉን አብራርተዋል፡፡
ኃላፊው አክለው በቀጣይ ከ20 ሺህ ችግኝ በላይ ለመትከል ዝግጅት መደረጉንና በተቋሙ ግቢ ያለው የመሬት አቀማመጥ በጥናት ተደግፎ ለውበት፤ ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚውሉ ችግኞች እንደሚተከሉ አብራርተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጳውሎስ አሚገሮ ከጂንካ ቅርንጫፍ
More Stories
የጋሞ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሐ ግብር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 23ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ
የጎፋ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሳውላ ከተማ ማካሄድ ጀመረ
የወላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው