በክልሉ በሚገኙ የግል ድርጅቶች ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ ስራተኞች መብታቸውና ጥቅማቸው ተከብሮ መስራት እንዲችሉ በማህበር መደራጀት እንደሚያፈልግ ተገለጸ
በክልሉ በሚገኙ የግል ድርጅቶች ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ ስራተኞች መብታቸውና ጥቅማቸው ተከብሮና ተጠብቆ መስራት እንዲችሉ በማህበር መደራጀት እንደሚያፈልግ በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን የደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ የሚገኙ ነባር ማህበራትን አቅም ለመገንባትና አዳዲስ ማሕበራትን ለማቋቋም ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ እንደሚሰራም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን በመላ ሀገሪቱ የነበሩትን ቅርንጫፎች ለማሳደግ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሚዛን አማን ከተማ ከመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ጽ/ቤት በመክፈት እየሰራ እንደሚገኝ የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ኢሳያስ አይሳ ገልጸዋል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ወደ ስራ ከገባ ወዲህ በክልሉ በሙሌጌ መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበርና በሙሌጌ አግሮ ኢንዱስትሪ መካከል የተፈጠረውን የህብረት ስምምነት ክርክር ለሁለት ዓመታት ቆይቶ የነበረውን በማስተካከል ወደ መስማማት እንዲመጡ መደረጉን ለአብነት አንስተዋል።
በክልሉ በሚገኙ ስድስት ዞኖች 28 የተደራጁ ማህበራት እንዳሉ አቶ ኢሳያስ አንስተው፤ ጽ/ቤቱ በክልሉ ስራ ከጀመረ ወዲህም 200 አባል የያዘውን አንድ ማህበር ማደራጀታቸውን አብራርተዋል።
በክልሉ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመኖራቸው ምክንያት በርካታ የግል ድርጅቶች ቢኖሩም በማህበር የተደራጁት ጥቂቶች መሆናቸውን አቶ ኢሳያስ ጠቁመው፤ በ2018 በጀት ነባር ማህበራትን አቅም ማጎልበት ያልተደራጁትን የማደራጀት ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ወሰኑ ወዳጆ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የዕለት ደራሽ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ