የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሔድ ጀመረ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሔድ ጀመረ

ሀዋሳ: ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በተለዩ ዘጠኝ አጀንዳዎች ዙሪያ በጥልቀት እንደሚመክር ተመላክቷል።

ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሔደው የምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ፥ ከምክር ቤት አባላት በተጨማሪ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

በጉባኤውም የ2017 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ አካላት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 አስፈፃሚ አካላት መሪ እቅድ፣ እና ሌሎች ተያያዥ አጀንዳዎች ቀርበው ጥልቅ ውይይት ይደረግባቸዋል።

ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ