የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ተጠናቀቀ
ባለፉት ሁለት ቀናት በታርጫ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቅቋል።
በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቅራቢነት የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የቀረቡ ዶክተር አብይ አንደሞን የምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የስራና ክህሎት ቢሮ ሆነው የተሾሙት ዶክተር አብይ አንደሞ በምክር ቤቱ ፊት ቆመው ቃለ መሃለ ፈጽመዋል።
ምክር ቤቱ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የቀረበውን የዳኞች ከዳኝነት ስንብት የቀረቡለትን ዝርዝር ሀሳብ የምክር ቤት አባላት በመምከር ውሳኔውን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ