የህብረ ብሔራዊነት ማሳያ የሆነው የህዳሴው ግድብ ዋንጫ በራስ አቅም የመቻላችን ምልክት ነው ሲሉ የደቡብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደሮች ተናገሩ
ይህን የተናገሩት የህዳሴው ግድብ ዋንጫ በዞኑ ማዕከል ዲመካ ከተማ በገባበት ወቅት ነው።
አስተያየታቸውን የሰጡን አንዳንድ አርብቶ አደሮች እንደገለፁት፤ የህዳሴው ግድብ ዋንጫ የህብረ ብሔራዊነት ማሳያ ምልክት ከመሆኑም በላይ በመተባበር እና በአንድነት ከተሰራ የማይረጋገጥ ልማት እንደሌለ ያየንበት ነው።
አክለውም ኢትዮጵያ ያለመቻል ትርክቶቿን የሰበረች በመተባበር በአንድነት ጀምሮ መጨረስን ያረጋገጠችበት የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች አሻራ ያረፈበት ግድብ በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልፀዋል።
ብድርና ዕርዳታ በመከልከል ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የማይነጥፍ ሀብት አውጥታ እንዳትጠቀም ለማድረግ አሉባልታ ቢረጭም ኢትዮጵያ አሁንም በጋራ ተጠቃሚነት መርህ በራሷ አቅም ገንብታ ለማስመረቅ በቅታለች ሲሉ ገልፀዋል።
አሁንም ቀሪ ሥራው ተጠናቆ ሪቫን እስኪቆረጥ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀው፤ በቀጣይም እንደ ህዳሴው ግድብ በሌሎች የልማት ዘርፎች የሚያደርጉትን ድጋፍና አንድነት እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ተጠናቀቀ
የህብረተሰቡን የመንገድ መሠረት ልማት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ገለፀ
የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራሙ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ ሀብት ማፍራት ለመቀየር ያለመ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ገለፀ