የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ

‎የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ ምክር ቤቱ በህገመንግስት የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም የአስፈፃሚ አካላትን አፈፃፀም ገምግሞ ግብረመልስ ሰጥቷል ብለዋል።

‎በግብርና ስራ የመጣውን ለውጥ ማስቀጠል እንደሚገባ ያነሱት አፈ ጉባዔው በትምህርት ረገድ የትምህርት ለሁሉም ንቅናቄን ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

‎በጉባኤው የ2017 በጀት አመት የአስፈጻሚ አካላት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትና ቀጣይ ዕቅድ ውይይት ይደረግበታል፡፡

‎በሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ በምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየት ተነስቶ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና በካቢኒያቸው ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

‎የምክር ቤቱ ጉባዔ በደቡብ ቴሌቪዥን፣ በድርጅቱ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ፌስቡክና ዩቲዩብ በቀጥታ ይሰራጫል፡፡

‎ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ