የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ እየተካሔደ ነው
ሀዋሳ: ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የአስፈፃሚ መ/ቤቶችን የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም ባቀረቡት ሪፖርት መነሻ ያደረገ ጥያቄና አስተያየት በምክር ቤት አባላት እየቀረበ ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ የአስፈፃሚ መ/ቤቶችን የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ምላሽና ማብራሪያ በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳብ እና አስተያየት በማቅረብ ላይ ናቸው።
ምክር ቤቱ በዛሬው መርሃ ግብር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡ ይሆናል።
በጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ አፈ-ጉባኤዎች፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች፣ የሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የዕለት ደራሽ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ