በበጀት ዓመቱ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በማተኮር መሰራቱን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ አስታወቀ

በበጀት ዓመቱ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በማተኮር መሰራቱን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ አስታወቀ

ቅርንጫፍ ጣቢያው በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።

የቅርንጫፍ ጣቢያው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ሳልልህ፤ በበጀት ዓመቱ ልዩ ትኩረት በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በማተኮር ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል፡፡

በሁሉም ዘርፎች በክልላዊና ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስትዋል።

ወጣቶች በሀገረ-መንግስት ግንባታ ያላቸውን ሚና፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን፣ የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት እንቅስቃሴዎችን፣ የአረንጓዴ አሻራን፣ የሌማት ትሩፋትንና ሌሎችንም በርካታ ጉዳዮችን በተመለከተ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አቶ ስንታየሁ አንስተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት የተሻሉ መሆናቸውን በመግለጽ፤ በቀጣይ መስተካከል ያሉባቸውን ጉዳዮችም ጠቁመዋል፡፡

ህብረተሰቡን ያሳተፉ ወቅታዊና ሚዛናዊ የሆኑ ዘገባዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በቀጣይ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን