በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የአርባምንጭ ቅርንጫፍ ጣቢያ ወቅታዊ እና ተአማኒ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አኳያ በትጋት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ
የአርባምንጭ ቅርንጫፍ ጣቢያ ጽህፈት ቤት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
ጣቢያው በጋሞ፣ ኮንሶ እና ጋርዱላ ዞኖች የሚገኙ 8 ብሄረሰብ ቋንቋዎች አማርኛን ጨምሮ በ9 ቋንቋዎች ማህበረሰቡን እያገለገለ ይገኛል።
በተካሄደው የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 ዕቅድ ግምገማ ላይ የጣቢያው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጉጃ ጉሜ፤ ተቋሙ በሚዲያ ቴክኖሎጂ፣ በሬዲዮና ቴሌቪዥን ዜናና ፕሮግራም፣ በንጋት ጋዜጣ ስርጭት፣ በማስታወቂያ እና በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡን አብራርተዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ ተቋሙን በቴክኖሎጂ እቃዎች ለማደራጀት እና ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን የሚመለከታቸው አካላት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።
2018 በጀት ዓመት በቀረበው ጠቋሚ ዕቅድ በ8 ብሄረሰብ ቋንቋዎች እንዲሁም በደቡብ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ አማራጮች ወቅታዊና አዝናኝ ዜና እና ፕሮግራሞችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን አስረድተዋል።
የተቋሙ ሠራተኞች ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና ወቅታዊ መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የተጀመረውን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የጣቢያው ምክትል ስራ አስኪያጅና የይዘት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ በሀይሉ ሙሉጌታ፣ የዘርፍ አስተባባሪዎች፣ አርታኢዎች፣ ተርጓሚዎች እና ሌሎች የተቋሙ ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: አማሮ አርሳባ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2018 በጀት ዓመት ከ2 ቢሊዮን 62 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ
ለሕዝቡ የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ
በነገው እለት እንደ ሀገር ለሚተከለው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም 1.6 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መዘጋጀታቸውን የምእራብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መልኬ ኬላጌ ተናገሩ