የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ከዞኑ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቡታጅራ ከተማ ወይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል
በዞኑ በልማት፣ በሰላምና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ በተሰሩ ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ጫካ በተገኙበት ከዞኑ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቡታጅራ ከተማ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።
ከዞኑ ምስረታ በኋላ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን መሠረት ያደረገ ንግግር ያደረጉት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፤ በዞኑ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የህዝቡን አብሮነት መሠረት ያደረጉ ሰራዎች በመሠራታቸው ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ውጤት መመዝገብ የሀገር ሽማግሌዎና የሀይማኖት አባቶች ወጣቶችን ለሰላም በማሰለፍ ያደረጉት አስተዋፅኦ የማይተካ መሆኑን አመላክተዋል።
በኦሮሚያ አጎራባች ወረዳዎች አመራሮች ጋር ቅንጅታዊ ስራ በመሠራቱ የህዝብ ለህዝብ ትስስሩ መጠናከሩን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ተናግረዋል።
በግብርና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢንቨስትመንት፣ በገቢ አሰባሰብ እና የሰንበት ገበያ በማስፋፋት የኑሮ ውድነትን ለማርገብ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር አንስተዋል።
በክልሉ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል የኮሪደር ልማት ስራዎች መኖራቸውን የዞኑ አስተዳደር የተናገሩ ሲሆን መድረኩ ከዞኑ ህዝብ ጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚረዳ መሆኑን አንስተዋል።
በዞኑ የተሰሩ ስራዎች ሰነድ በመቅረብ ላይ የሚገኙ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: ፋሲል ሀይሉ
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከዞን እስከ ወረዳ የህዝቡን አስተያየት መሠረት በማድረግ በተሰራው ስራ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተፈቱበት በጀት አመት ነበር ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ
ወጣቱ ከሀገር ተረካቢነት ባለፈ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ለሀገሩ ለውጥ መስራት እንዳለበት ተገለጸ