የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ክህሎት መር የሆነ የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ አበባየው ታደሰ(ዶ/ር) ገለፁ
የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ የስልጠና ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ ግብአቶችን ለተመረጡ ኮልጆች ድጋፍ አድርጓል።
የስልጠና ግብአቶቹም በ2017 በጀት በተቋማት ማሽነሪ ግዢ ካፒታል ፕሮጀክት የተገዙ መሆኑም ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ አስተዳደር እና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ሃላፊ አበባየሁ ታደሰ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች ክህሎት መር የሆነ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ወሳኝ በመሆናቸው የተደረገው ድጋፍ አበረታች ነው።
አክለውም ከክልሉ መንግስት ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር ኮሌጆች የራሳቸውን አቅም መገንባትና የመገልገያ ቁሳቁሶችን በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ፤ ተቋሙ በሀገር ደረጃ ብቁ፣ ተመራጭና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን በማፍራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በክልሉ የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች አብዛኛው የግብአት ችግር ያለባቸው በመሆኑ ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት ይረዳ ዘንድ ክልሉ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነው አቶ አብዮት የገለፁት።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የሰልጣኝ አሰልጣኝ ኃላፊ አቶ ዳዊት ፋንታዬ፤ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች የሀገሪቱን ብልፅግና የሚያሳልጡ የሰው ሃይል የምናፈራበት በመሆናቸው በቂ ግብአት ያለው ተቋም መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
የተቋማትን የግብአት ችግር ለመቅረፍ በተደረገው ጥረት በክልሉ ከሚገኙ 12ቱ ዞኖች ለተውጣጡ ለ17 ኮሌጆች በ11 ሚሊየን 325 ሺህ 400 ብር ከመንግስት በተገኘ ድጋፍ 55 የልብስ ስፌት ማሽን እና 66 ኮምፒውተሮች ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።
ተሳታፊዎችም የተደረገው ድጋፍ የነበረውን ችግር በማቃለል ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት የእንደሚያግዝ ገልፀው የሚገኙ ውስን ሀብቶችን በአግባቡ መጠቀም አለብን ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ክህሎት መር የሆነ የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ አበባየው ታደሰ(ዶ/ር) ገለፁ

More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ከዞኑ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቡታጅራ ከተማ ወይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል
ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከዞን እስከ ወረዳ የህዝቡን አስተያየት መሠረት በማድረግ በተሰራው ስራ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተፈቱበት በጀት አመት ነበር ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ