በክልሉ የህዝብ ለህዝብና የመንግስት ትስስርን ለማጠናከር የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች በመሆናቸውን ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ
ቋሚ ኮሚቴው የክልሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ በዚህ ወቅት እንደገለፁት፤ የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም በክልሉ የህዝብ ለህዝብና የመንግስት ትስስርን ለማጠናከር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡
በዚህም የመንግስት የልማት እንቅስቃሴ በአግባቡ በሚዲያ ተደራሽ ማድረግ ይገባል ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ፤ ሚዛናዊና ወቅታዊ መረጃዎችን ማቅረብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቀነስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የገለፁት ሰብሳቢው፤ በሂደቱ ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባም አስገነዝበዋል፡፡
የዘርፉን አመራርና ባለሙያ ሀገራዊ፣ አለም አቀፋዊና አሁናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በአግባቡ እንዲረዱ አቅም ማሳደግ እንደሚገባም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየት የቢሮ ሃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በቢሮው ሀሰተኛ መረጃዎችን በመከላከል የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ሃላፊው አስረድተዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ ሚዲያዎችን አቅም የማሳደግ ስራ እየተሰራ ከመሆኑም በሻገር ከሌሎችም ሀገራዊ የሚዲያ ተቋማት በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ከዞኑ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቡታጅራ ከተማ ወይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል
ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከዞን እስከ ወረዳ የህዝቡን አስተያየት መሠረት በማድረግ በተሰራው ስራ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተፈቱበት በጀት አመት ነበር ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ