የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረ መምጣቱን በጌዴኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የከተማ አስተዳደሩ የተጀመረውን ሀገራዊ የልማት ኢንሼቲቭ በማስቀጠል የሕብረተሰቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
አቶ ማሙሽ ካሱና ገብረማርያም ሎኮ የከተማው ነዋሪዎች ሲሆኑ የኮሪደር ልማት በማልማት ሕዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ የሀገሪቱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በመግለጽ ልማቱን ማስፋፋት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ የጎላ በመሆኑ መንግስት በዘርፉ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጨለለቅቱ ከተማ ከተቆረቆረች 59 ዓመታትን ብታስቆጥርም በዕድገትና ልማት ወደኋላ ተጓትቶ መቆየቱን ተናግረው በአሁኑ ጊዜ በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረ በመምጣቱ መደሰታቸውን አስረድተዋል።
ከተማን ለነዋሪዎች ማራኪና ምቹ ለማድረግ፣ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባው አብራርተው ከማስተር ፕላን ውጪ የሚከናወኑ ሕገወጥ ግንባታዎችንና የመሬት ወረራ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል ይገባል ብለዋል።
ልማቱ የከተማውን ውበት ከማስጠበቅና ምቹ ሥነ-ምህዳር ከመፍጠሩም ባሻገር ለልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን የሚናገሩት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ይጨነቁ ዋቆ ናቸው።
ነዋሪዎቹ አክለውም ከተማውን ለማልማት በሚደረገው እንቅስቃሴ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት እያደረጉ ያሉት የልማት ተነሳሽነትና ትብብር አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ከመንግሥት ጎን በመሰልፍ በማናቸውም ልማታዊ ስራዎች ላይ የነቃ ታሳትፏቸዉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል።
የጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተስፋነ ታደለ እንደተናገሩት፥ በብልጽግና ፓርቲ አማካኝነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ኢንሼቲቭን ተግባራዊ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
የጨለለቅቱ ከተማን ከሌሎች ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ፕላን የማስጠበቁን ሥራ ጨርሰው ከተማ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን በቁርጠኝነት ወደ መሥራት መገባቱን አስታውቀዋል።
በከተማው ሥራውን ለማስጀመር የሚሆን 6 ሚሊዮን ብር ከሕብረተሰቡ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ባለሀብቶች በማስተባበር ሥራ መጀመሩን የጠቆሙት ከንቲባው፥ ከተማዋን ለነዋሪዎቹ ምቹና ማራኪ አድርጎ ለማስዋብ የተጀመረውን ተግባር ሁሉም መደገፍ እንደሚገባው አሳስበዋል።
በአሁኑ ጊዜ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በማፋጠን ሕብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ያላሰለሱ ጥረቶች መኖራቸውን ጠቁመው ባለድርሻ አካላት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፡ እስራኤል ብርሃኑ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ #ደሬቴድ፣ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም
የጤናው ዘርፍ አገልግሎት ለማጠናከር የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስገነዘበ