የገጠር ኮሪደር ልማት ከሌማት ቱርፋት ጋር በማስተሳሰር የአርሶአደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 06/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የገጠር ኮሪደር ልማት ተግባር ከሌማት ቱርፋት ጋር በማስተሳሰር የአርሶአደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ የደቡብ ምእራብ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ።

የጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤት ከተባባሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በቤንች ሸኮ ዞን ጉረፈርዳ ወረዳ የገጠር ኮሪደር ተግባራትን አስጀምረዋል።

በከተማ እየተከናወነ ካለው የኮሪደር ልማት ተግባራት ባለፈም የገጠር የኮሪደር ልማት ተግባራት እንደ ሀገር እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል። በደቡብ ምእራብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ጉረፈርዳ ወረዳ የጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤት ከተባባሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፍቃድ እና የገጠር ኮሪደር ልማት ፕሮግራምን ባስጀመሩበት ወቅት፥ የደቡብ ምእራብ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደተናገሩት በከተማ ከሚከናወኑት የኮሪደር ልማት ተግባራት ባሻገር የገጠር ኮሪደር ልማት ሌላኛው ተግባር መሆኑን ጠቅሰው ከመንገድ ማስፋት ባለፈም ተግባሩ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፥ የገጠር የኮሪደር ልማቱን ተግባር ከሌማት ቱርፋቱ ጋር በማስተሳሰር አርሶ አደሩ በግቢው ዶሮ በማርባት፣ ንብ በማነብ፣ የጓሮ አትክልት በማልማት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ሊያጎላው ይገባልም ብለዋል።

አርሶ አደሩ ውብ እና ጽዱ አከባቢ በመኖር እራሱን እና ቤተሰብን ከተለያዩ በሽታዎች መጠበቅ ይገባዋል ያሉት ርእሰ መስተዳደሩ፥ በተለይ በኮሪደር ልማቱ የከብቶችን መኖሪያ ከሰው መኖሪያ ለመለየትም እንደሚያስችል ገልጸው፥ የፍራፍሬ ምርቶችን በግቢው በማምረት የገቢ አቅሙን ማሳደግም ይችላል ብለዋል። ይህ ተግባር ተጠናክሮ ከቀጠለ በተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚቻል ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤት የተቋማት ክትትል እና የካቢኒዎች ጉዳይ ሚኒስተር ዴኤታ አቶ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው፥ በክረምት ከሚከናወኑ የበጎ ተግባራት ባለፈ የገጠር ኮሪደር ልማትን ማስጀመር ማጠናከር ዋናው አላማ አድርገው እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው፥ ለዚሁ ማሳያ ያሉት አቶ አክሊሉም በጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤት እና በተባባሪ አካላት በደቡብ ምእራብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በጉረፈርዳ ወረዳ የሚገነቡት አምስት ሞዴል ቤቶች አቅመ ደካማዎችን ከመደገፍ ባለፈም የገጠር ኮሪደል ልማት ማሳያ ሞዴል ቤቶች እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

አርሶ አደሩም በግቢው ውስጥ የተለያዩ ኢኮኖሚ የሚያመነጩ ተግባራትን በማከናወን እራሱንም ቤተሰቡንም ሊለውጥ እንደሚገባም አቶ አክሊሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን