በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ ወጀባቴ ቀበሌ ንቡር ሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፈት ሆነ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ ወጀባቴ ቀበሌ ንቡር ሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፈት ሆነ

ጤና ኬላው በመንግስትና ህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባ ሲሆን በአጠቃላይ 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ፈጅቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአንድ ወረዳ ኢኒሼቲቭ ማዕከል የሆነው ይህ ሁሉ አቀፍ ጤና ተቋም፤ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ፣ የዞኑ እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ፤ በእለቱ የተመረቀው ንቡር ሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ በክልሉ በተጠናቀቀዉ በጀት አመት ከተገነቡት 17 ጤና ኬላዎች አንዱ ነው ብለዋል።

የህብረተሰቡ የዘመናት ጥያቄ የሆነው ይህ ሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ በጥራት የተሰራ መሆኑን አንስተው ሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በአምስት ወራት ግንባታዉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ የአካባቢው ነዋሪዎች በገንዘብ እና በጉልበት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ከዚህ ቀደም በአካባቢው የህክምና ማዕከል ባለመኖሩ እናቶች በወሊድ ምክንያት ይሞቱ እደነበር ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል።

የያነጋገርናቸዉ እናቶች ይህ ሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ ከዚህ ቀደም ይገጥማቸዉ የነበረዉን እንግልት ሊቀርፍላቸዉ እደሚችል ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡ አልማዝ ቢረዳ