ሀዋሰ፡ ሐምሌ 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ወጣቱ በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ሀለንተናዊ ዕድገትና ለውጥ እንዲያመጣ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የጎፋ ዞን አስተዳደር ገለጸ።
የዓለም የስነ ህዝብ ቀን “ወጣቱን የማህበረሰብ ክፍል ማብቃት በተስፋ የተሞላ የተሻለ ቤተሰብ እና ዓለም መፍጠር ነው” በሚል መሪ ቃል በጎፋ ዞን በፓናል ውይይት ተከብሯል።
በዓለም ለ35ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ የስነ ህዝብ ቀን በተከበረበት ወቅት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ከኢኮኖሚ እድገት ጋራ ያልተመጣጠነ የሕዝብ ቁጥር መጨመር ለሚያስከትለው ቀውስ ዋናው መንስኤ በስነ ህዝብ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ አለመስራት ነው ብለዋል።
የአንድ ሀገር ትልቁ ሀብት ህዝብ በመሆኑ በተለይም የወጣቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።
ያልተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር መጨመር የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቀነስ በስነ-ህዝብ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
የህዝብ ዕድገትን ዕድል አድርጎ መጠቀምና ተቋማዊ ቅንጅት በመፍጠር የሚታዩ የቅንጅት ጉድለቶችን ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል።
የስነ-ህዝብ ተግባራትን ለይቶ በትኩረት በማቀድ በግብርና፣ በትምህርት፣ በስነ ልቦና ብቁ የሆነ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በትኩረት መስራት እንደለበት ተናግረዋል።
የዞኑ ፕላንና ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙሉቀን ጉጃ በበኩላቸው ወጣቶች የእምቅ ሀይል ባለቤት በመሆናቸው ፍላጎታቸውን በማጥናት ዕውቀታቸውን እና የሙያ ክህሎታቸውን ማሳደግ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸት ይገባል ብለዋል።
በዞኑ የሚገኙ ወጣቶችን በሥነ ምግባር አንጾ፥ የሥራ ባህላቸውን ይበልጥ በማሳደግ ከራስ አልፎ ለዞኑ ሁለንተናዊ ለውጥ የበኩላቸውን አሰተዋእጾ የሚያበረክቱ ወጣቶችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ያልተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር መጨመር የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቀነስ በስነ-ህዝብ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
ለወጣቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ስነ-ህዝብ ቀንን አስመልክቶ ለውይይት መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያዬት የወጣቶችን ስብዕና ማዕከላት በማስፋፋት በተለያዩ የሥራ አማራጮች በማሰማራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ከጠልቃ ገብነት፣ ከዕንግልትና ገንዘብ ብክነት በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በዞኑ በሚኖረው ቆይታ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለፀ
ከ14 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሠማራታቸው ተገለጸ