የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በዞኑ በሚኖረው ቆይታ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለፀ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በጎፋ ዞን የነበረውን ቆይታ በማጠናቀቅ ወደ ባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ሲገባ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬዉ ፍሻለዉ በአቀባበሉ ወቅት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ መቃረቡን አንሰተው ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አሻራውን ለማስቀመጥ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘርፉ አጥናፉ ከዓለም 7ኛ ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ የህዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ይሁን ደምሴ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአድዋ ድል ቀጥሎ ኢትዮጵያን ከፍ ያደረገ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል።
የባስኬቶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ የህዳሴው ግድብ ገቢ አሰባሰብ አቢይ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ ወንዳፍራሽ ንጉሴ፤ ዋንጫው በዞኑ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚኖረው ቆይታ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስረድተዋል።
የግድቡ ሥራ ሊጠናቀቅ በመቃረቡ መደሰታቸውን የገለጹት የዞኑ ነዋሪዎች፤ ቀሪ ሥራዎችን ለመጨረስ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ወጣቱ በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ሁለንተናዊ ዕድገትና ለውጥ እንዲያመጣ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ
ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ከጠልቃ ገብነት፣ ከዕንግልትና ገንዘብ ብክነት በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ከ14 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሠማራታቸው ተገለጸ