“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 04/2017 ዓ.ም (ደረቴድ) በወላይታ ዞን “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ወጣቶች በበጎ አገልግሎት ላይ በስፋት እንዲሳተፉ በማድረግ የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ችግሮች በመፍታት የበጎ ፈቃደኝነት ባህል ለማጎልበት ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

በዞኑ ዘንድሮ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ከ912 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል።

በዚህም ከ572 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ እና ከ550 ሚሊዮን 851 ሺህ በላይ የሚገመት ሀብት በወጣቶች ጉልበት ለማዳን ግብ ተጥሎ ይሰራል።

በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታ፥ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊና የወጣት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማርቆስ ማቴዎስ፣ የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ መስፍን ቶማስን ጨምሮ የዞን ማዕከል አጠቃላይ አመራሮች፣ የበጎ ፈቃድ ወጣቶችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን