2ኛ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 01/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) 2ኛ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳዉሮ ታርጫ ካምፓስ እየተሰጠ ነው፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በበይነ መረብ እየተሰጠ ይገኛል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አባተ ኡቃና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተው ፈተናውን በይፋ አስጀምረዋል።
የዘንድሮ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እየተሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በክልሉ 19 ሺህ 127 ተማሪዎች በፈተናው ከሚቀመጡ መካከል 9ሺህ 758 ተማሪዎች የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች ናቸው።
ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል ከ3 ሺህ በላይ በወላይታ ሶዶ ዳዉሮ ታርጫ ካምፓስና ታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመፈተኛ ክፍሎች ተዘጋጅተው ፈተና እየተቀበሉ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አባተ ኡቃ ተናግረዋል።
በታርጫ ፈተና ማዕከላት በበይነ መረብ 151 እየተፈተኑ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
ተፈታኞቹም ከግልና መንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በርቀት ትምህርት የዘመኑን ትምህርት መከታተላቸውንም በመጠቆም።
ከትምህርት ሚኒስቴር የዳዉሮ ታርጫ ካምፓስ የፈተና ማዕከል ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ አየለ እንደገለጹት የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ተፈታኞች በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን በመጥቀስ የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍም በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን ገልጸዋል።
በበይነ መረብ ለሚፈተኑ ተማሪዎችም በቂ የኮምፒዩተርና የመፈተኛ ክፍል መዘጋጀቱንም አስረድተዋል።
በወረቀት ለሚፈተኑ በበቂ ሁኔታ ስርጭት መደረጉንም ገልጸዋል።
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዳዉሮ ታርጫ ካምፓስ ዲን መምህር መብራቱ ለገሰ በበኩላቸው የፈተናውን ደህንነት በማስጠበቅ ሂደቱ በተሻለ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ሌሎችም የደህንነት ማስጠበቂያ ሥራዎች ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ በጥንቃቄ እንደሚያከናወኑም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋል እንዲችሉና ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ የተሻለ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳደር ገለፀ
የሚገነቡ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ