ከተሞችን ለነዋሪዎች ጽዱ፣ ውብና ምቹ ለማድርግ በቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ሥርዓት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ አሳሰበ
ቢሮው የክልሉ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንሰቲትዩት ተቋም ጋር በጋራ በቆሻሻ አወጋገድ ጥናት ዙሪያ ምክክር መድረክ አካሂዷል።
በክልሉ ባሉ በ 6 ከተሞች የቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጉድለት መኖሩ በጥናቱ ተረጋግጧል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በከተሞች ውስጥ በተለያየ መልክ የሚመመነጩ አደገኛ ቆሻሻዎች መኖራቸውን ጠቅሰው በጥንቃቄና በአግባቡ ካልተወገዱ በከተሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ ገልፀዋል።
ቆሻሻ በአግባቡ ባለመወገዱ ለአካባቢ ብክለትና፣ ጎርፍ እና የተለያዩ በሽታዎች አየተከሰቱ በመሆናቸው ከተሞችን ለነዋሪዎች ፅድና ምቹ ለማድረግ ሁሉም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ጥናት ምርምር የኢኮኖሚ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታምራት አሰፋ በበኩላቸው ቆሻሻ ከማመንጨት ጀምሮ አወጋገድ ሥርዓት ላይ ያተኮረ ጥናት በክልሉ 6 ከተሞች መካሄዱን ገልጸዋል።
በተለይም ከከተሞች መስፋፋትና የህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የሚፈጠረው የቆሻሻ መጠን መጨመር በአከባቢ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ በህግ አግባብ ለመምራት የሚያስችል ጥናት ነው ብለዋል።
በመድረኩ በቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ዙሪያ ጥናት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን መድረኩ በጥናቱ ማሻሻያ ላይ ሀሳብ ተነስቶ ምላሸ ተሰጥቶበታል።
ዘጋቢ፡ አለሚቱ አረጋ
More Stories
የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋል እንዲችሉና ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ የተሻለ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳደር ገለፀ
2ኛ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው