የህዝቦችን የመበልፀግ ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ግብርን በአግባቡ በመክፈል ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አሳሰበ
ሀዋሳ፣ ሐምሌ 01/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝቦች የመበልፀግ ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ግብር በአግባቡ በመክፈል ሁሉም ሀላፊነቱን ልወጣ ይገባል ስሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የግብር መክፈያ መርሃ ግብር በጌዴኦ ዞን በይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር በይፋ ተጀምራል።
ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ እንደተናገሩት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የህዝባችን የመልማት ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል ።
የህዝቦችን የመልመት ፍላጎት የሚሳካውና ሀገራችን የጀመረችው የለውጥ ጉዞ እውን ሊሆን የሚችለው ከታክስ ስወራና ማጭበርበር የፀዳ የግብር አከፋፈል ስርዓት ሲኖር መሆኑን ወ/ሮ አለምነሽ ተናግረዋል።
የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር)፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በተገበረችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት በራስ ገቢ እራስን ማስተዳደር መቻሉን ጠቅሰው ግብር ለሁሉም የልማትና መልካም አስተዳደር መሠረት በመሆኑ ሁሉም ግብር ከፋይ በታማኝነት ሊከፍል ይገባል ብለዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌቱ ታምሩ፣ በዞኑ የግብር መሰብሰብ አቅም መጨመሩን ገልጸው በዘንድሮ የግብር መክፈያ ወቅትም ከ8 ሺህ በላይ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች 1.6 ቢልዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል።
የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታደለ ጥላሁን የዘንድሮን ግብር አከፋፈል ከተማችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በልማት፣ በኢንቨስትመንት እና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ በተሰራ አመርቂ ስራ የፈርጅ 1 ጀረጃን በያዘችበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ከግብር ከፋዮችም፣ ግብርን በወቅቱ በመክፈላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ሌሎችም በጊዜና በአግባቡ ግብራቸውን ሊከፍሉ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ : ወርቅአገኘሁ ወልደየስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ደም መለገስ ለተጎዱ ወገኖች ህይወትን መስጠት፣ የአይን ብሌን መለገስ ደግሞ የህይወት ብርሀን መመለስ መሆኑ ተገለፀ
የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋል እንዲችሉና ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ የተሻለ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳደር ገለፀ