በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 የግብር ወቅት ከደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለጸ
የቢሮ ሀላፊዋ በ2017 የግብር መክፈያ ንቅናቄን አስመልክቶ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ በመግለጫቸው እንዳሉት፤ በክልሉ የተጀመሩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ለማሳለጥ ገቢ ወሳኝ መሆኑን አስታወሰው፤ በዘንድሮ የግብር አሰባሰብ ወቅት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ከሐምሌ 1 ጀምሮ የ’ሐ’ የግብር ከፋዮች ከነገ ሐምሌ ጀምሮ በይፋ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ይደረጋል።
በዚህም የ2017 የግብር ዘመን የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው እንዲያጠናቅቁ የቢሮ ሀላፊዋ አሳስበዋል።
በንቅናቄው 1 ቢሊዮን ብር ገቢ ከደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች እንደሚሰበሰብ አውስተው 230 ጊዜያዊ የታክስ መሰብሰቢያ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ወ/ሮ አለምነሽ ተናግረዋል።
በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ያሳሰቡት የቢሮ ሀላፊዋ፤ በተለይም 83 ሺህ የ’ሐ’ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን ባሉበት ሆነው በቴሌ ብር መክፈል እንዲችሉ ቅደመ ዝግጅት ሥራ መከናወኑንም አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል