የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

‎የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋይ ነጋዎችን ዓመታዊ ግብር በ7 ቀን ሰብስቦ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

የደቡብ ኦሞ ‎ዞን የ2017 የግብር ዘመን ክፍያና የ2018 የንግድ ፍቃድ ዕድሳት ማስጀመሪያ ልዩ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

‎ባለፈው የግብር ዘመን በገቢ አሰባሰብ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የገቢ መዋቅርና ግብር ከፋዮችን ያመሰገኑት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ፤ የውስጥ ፍላጎቶችን ለማሟላት ያሉ የገቢ አማራጮችን አማጦ መሰብሰብ ግዴታ በመሆኑ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋይ ነጋዴዎች በመንግስት የተወሰነባቸውን ግብር በተቀመጠው ቀን ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት መምራት አለባቸው ብለዋል።

‎የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ በቀለ የ2017 የግብር ዘመን ግብር አሰባሰብና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ በተመለከተ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፤ በዞኑ ውስጥ ካሉ 5 ሺህ 3 መቶ 95 የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 1 እስከ 7 ባሉ ተከታታይ ቀናት 21 ሚልየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ነው።

‌‎የደቡብ ኦሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ሁሉአገር አልቴ ; የንግዱ ማህበረሰብ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ ግብሩን በሚከፍልበት ወቅት የ2018 የንግድ ፈቃድ ምዝገባና እድሳት እንደሚደረግ አንስተዋል።

‎የመድረኩ ተሳታፊዎች ግብር ከፋዮች በተቀመጠላቸው ወቅት ግብራቸውን እንዲከፍሉ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

‎2 ሺ 5 መቶ የሚሆኑ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በቴሌ ብር፤ ሲስተም ያልተዘረጋባቸው ወረዳዎች ደግሞ በማንዋል ግብራቸውን እንደሚከፍሉ ተመልክቷል።

‎ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን