በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ
በክልሉ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብ በቤንች ሸኮ ዞን ሼይ ቤንች ወረዳ ጋይሼማ ቀበሌ ተጀምሯል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ ክልል አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በይፋ ተጀምሯል።
ሀገራችን ከተረጂነት ተላቃ በምግብ እራሷን እንድትችል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ወሳኝ ነው ብለዋል።
በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 400 ሚሊዮን የሚጠጉ ችግኞች በ3800 ችግኝ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በክልላዊ የተከላ መርሐ ግብር በነቂስ በመሳተፍ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው እንደተናገሩት፤ በክልሉ ባለፉት 6 አመታት ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል፡፡
በተያዘው በክረምት ተከላ ወቅት 196 ሚሊየን 726 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ በቂ ዝግጅት መደረጉን አንስተው፥ ከእነዚህ ውስጥ 60 በመቶ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውን አብራርተዋል።
ባለፉት አመታት የተተከሉ ችግኞች የፅድቀት መጠን 86 ከመቶ መድረሱንም ገልጸዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን በበኩላቸው፤ ለግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት መጨመር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ጦያር ይማም – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ከዞኑ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቡታጅራ ከተማ ወይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል
ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከዞን እስከ ወረዳ የህዝቡን አስተያየት መሠረት በማድረግ በተሰራው ስራ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተፈቱበት በጀት አመት ነበር ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ