ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የልማት ዘርፍ ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ መምጣቱን የዳዉሮ ዞን ግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ልማት መምሪያ አስታወቀ
በዞኑ የመኸር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በዞኑ ዲሣ ወረዳ ጋቶ ጉፎ ቀበሌ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ተካሂዷል።
በዞናዊ የማስጀመሪያ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተገኙ የቀበሌው ነዋሪዎች እንደሚሉት፤ ከዚህ ቀደም በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራዎች ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ ይገኛሉ።
ከዚህ በመነሣት የተያዘውን የክረምት መርሃ ግብር የአረንጓዴ አሻራ ለማሣካት የተቻለውን ሁሉ እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል።
የዲሣ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወርቁ ዲዳና በበኩላቸው፤ በወረዳው በሚገኘው 16 ቀበሌያት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በወረዳው 3.9 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን ቀጣይ ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ከ6 መቶ ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንም አስረድተዋል።
የዞኑ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና የኅብረት ሥራ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ በተላ በየነ በበኩላቸው፤ እንደ አገር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጫና መቋቋም እንዲቻል የተጀመረውን ዕቅድ ለማሣካት ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ውጤት እያስገኘ ይገኛል ብለዋል።
ከዚህ በመነሣት በዞን በበልግና በመኸር የእርሻ ወቅት ቡና፣ እንሰትና የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞችን ጨምሮ ከ75 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል የታቀደ ሲሆን በአንድ ጀምበርም 7.5 ሚሊዮን የተለያዩ ዓይነት ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንም አስረድተዋል።
ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የአርሶአደሩን ሕይወትና ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ መምጣቱንም ተናግረዋል።
ከተገኘው ለውጥ መነሻ በሁሉም አካባቢዎች ለአረንጓዴ አሻራ ልማት ትኩረት መደረጉንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የክልሉን አስፈፃሚ አካላት አመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሁለተኛ ቀን ውሎ እንደቀጠለ ነው