የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የክልሉን አስፈፃሚ አካላት አመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሁለተኛ ቀን ውሎ እንደቀጠለ ነው
ሀዋሳ: ሰኔ 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉ ምክር ቤት ህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ የፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሚከታተሏቸዉን ቢሮዎችና ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ ዛሬም በማካሄድ ላይ ናቸው።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ የደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ፣ የሠላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የንግድ ገበያ ልማት ቢሮ በዛሬው የጠዋት መርሐ ግብር ሪፖርታቸውን ለአራቱም ቋሚ ኮሚቴዎች በማቅረብ ላይ ናቸው።
ሌሎች ሴክተር መስሪያቤቶችም በወጣላቸው ፕሮግራም መሠረት የሚያቀርቡ ሲሆን፥ የአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ እስከ ሰኔ 29/2017 የሚቀጥል ነው።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ23ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 347 ተማሪዎችን አስመረቀ
በ2018 በጀት ዓመት የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል – አቶ ፍቅሬ አማን
ሚዲያን ለአዎንታዊ ነገር በመጠቀም ወጣቱ ሀገርን መገንባት አለበት – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን