በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚገኙ አገራዊና ክልላዊ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራ ማሳረፍ መርሐ ግብር አከናውነዋል ።
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ቢሮ ኃላፊና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት እዮብ እንደተናገሩት በክልሉ በነገው ዕለት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በይፋ በሚጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አስቀድሞ የሚዲያ ባለሙያዎች ችግኝ በመትከል በሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎች በአረንጓዴ አሻራ ወቅት ኩነቶችን ለህዝብ ከማድረስ ባለፈ ችግኝ በመትከል ሀገራዊ አሻራቸውን ማኖር ይገባቸዋልም ብለዋል።
የደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ትዕዛዙ ኬንጫ እንደገለፁት የሚዲያ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ዘንድሮ በተለየ መልኩ የችግኝ ተከላ መርሐግብሩ ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ በመቻላቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
የችግኝ ተከላው ለአከባቢው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመግለጽ በየጊዜው ከሚከናወነው ተከላ ባሻገር የተተከሉትን እንክብካቤና ጥበቃ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ግብሩ ላይ የተሳተፉ የሚዲያ ባለሙያዎች በበኩላቸው ዕድሉን አግኝተው አሻራቸውን በማኖራቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎች እያደረጉ ያሉት የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።
በመርሐግብሩ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚንኬሽን ተቋማት ባለሙያዎችና እንዲሁ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሚዛን ቅርንጫፍ አመራርና ሰራተኞች ተሳታፊዎች ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ጦያር ይማም ከሚዛን ቅርንጫፍ
More Stories
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው
በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።
ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና የምርምር ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ አስታወቀ