የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋማትን የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ዕቅድ አፈፃፀም መገምገም ጀመረ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋማትን የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ዕቅድ አፈፃፀም መገምገም ጀመረ

ሀዋሳ: ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጤና፣ ትምህርት ቢሮ፣ የቴክኒካና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ እንዲሁም የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮን የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ እቅድ የስራ ትግበራ ይገመግማል።

ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው የጠዋት መርሐ-ግብር የክልሉን ጤና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ዕቅድ አፈፃፀም የተከናወኑ ተግባራት በአስፈፃሚ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን በሚቀርበው አፈፃፀም ዙሪያ ጥያቄና ግብረ መልስ የሚሰጥባቸው ይሆናል።

በበጀት ዓመቱ የስራ አፈፃፀም ግምገማም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙን ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ የተቋማት የቢሮ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ