የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት አመት የአመቱን የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ነ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት አመት የአመቱን የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ነው

ሀዋሳ: ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት አመት የአመቱን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር መመልከት ጀምሯል።

የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት አመት የአመቱን ሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አንዷለም አምባዬ ናቸው።

በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት የተለያዩ ጥያቄና አስተያየት የቢሮ የስራ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዱንጋ ናኩዋ ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የተቋማቱ የቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት እየተሳተፉ ነው።

ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ