በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ በተሠራው የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ሥራ የተሻለ ውጤት መምጣቱን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ገለጸ
የወረዳው ነዋሪዎች በበኩላቸው ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በመስራቱ ሠላማዊ አከባቢ እየተፈጠሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የወናጎ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር መብራቱ ቅልጡ እንደተናገሩት፤ በወረዳው ባለፉት ጊዜያት የንጥቂያና ስርቆት ወንጀል ድርጊቶች እንነበሩና ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር በሠራው የማህበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ሥራ የወረዳውን ሠላም ማስጠበቅ ተችሏል፡፡
በወረዳው በሚገኙ በ16 ቀበሌያት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተሠራ መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር መብራቱ ገልፀዋል።
የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በየጊዜው ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የቡና ጠጡ መርሃ ግብር በማዘጋጀት በወንጀል መከላከል ዙሪያ የመመካከር ልምድ እየዳበረ በመምጣቱ የተሻለ ውጤት መገኘቱን አስረድተዋል።
ከዚህ ቀደም ሲፈፀሙ የነበሩ የንብረት ስርቆት ወንጀል ተቀርፎ የቡና፣ የእንሰትና የመሳሰሉት ምርት ያለምንም ችግር በመሰብሰብ ተጨባጭ ለውጥ ማየት መጀመራቸውን በወረዳው ሞኮኒሳና የካራ ሶዲት ቀበሌ ነዋሪዎች ገልፀው በዚህም የወረዳው ፖሊስ አባላት ከሌሎች ፀጥታ አካላት ጋር ወንጀሉን ለመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
ነዋሪዎቹ አክለውም ትውልድን በስነምግባር አንጾ ማሳደግ እና የወንጀልን ተግባር ከቤተሰብ ጀምሮ መከላከል የእያንዳንዱ ግለሰብና ቤተሰብ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በወንጀል ተይዘው ለህግ በሚቀርቡ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባም ነዋሪዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘጋቢ፡- ዘርሁን ሹፌር – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በክልሉ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራ አሳረፉ
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው
በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።