የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሠላም፣ የአንድነት እና የልማት ኮንፈረንስ ሁለተኛ ቀን ውሎ መካሄድ ጀምሯል
ሀዋሳ: ሰኔ 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሠላም፣ አንድነት እና የልማት ኮንፈረንስ ሁለተኛ ቀን ውሎ የዕለቱ የክብር እንግዳ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች የሠላም፣ የአንድነት እና የልማት ኮንፈረንስ፥ በክልሉ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።
መድረክ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ በየደረጃው ከሚገኙ መዋቅሮች የተወጣጡ የክልሉ ተወላጅ ምሁራንና ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።
“ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ኮንፈረንስ በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ከ 1 ሺ በላይ ተሳታፊዎች በመካፈል ላይ ናቸዉ።
ኮንፈረንሱ በሁለተኛ ቀን ዉሎዉ የክልሉን አንድነት የሚያጠናክሩ ተቋማዊ አደረጃጀቶችና ፎረሞች ምስረታን ጨምሮ በቀሪ ጉዳዮች ላይ በመምከር ዉሳኔዎች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-