የህብረት ስራ ማህበራት ለግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያበረክቱት አስታዋጾ ከፍተኛ በመሆኑ አውቆ ትኩረት ስጥቶ ሊሰሩ እንደሚገባ የማዕከላዊ እትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ ከምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለቅመማ ቅመም ምርት ዘላቂ የገበያ ትስስር ለመፈጠር ከአምራች ህብረት ስራ ማህበራትና ኢንተርፕራይዝ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በክልሉ በተበታተነ መልኩ እየለማ የሚገኘው የሮዝመሪ ምርት በህብረት ስራ ማህበራት በስፋት እየለማ በመሆኑ ክልሉና ሀገሪቱ ከዘርፉ መግኘት የሚገባቸውን ጥቅም በማግኘት ላይ እንደሆነ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የግብርና እና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር የተናገሩት።
በዚህ ዘርፍ የታየው ውጤታማነት በሌሎችም በግብርና መስክ የተሻለ ምርትና ምርታማነትን አምርቶ ለዓለም ገበያ በስፋትና በጥራት ለማምራት የህብረት ስራ ማህበራት አውቆ ማምራት አስፈላጊ መሆኑን ነው ኃላፊው የገለጹት።
በመድረኩ ለይ ከጉራጌ፣ከምስራቅ ጉራጌ፣ከስልጤ እና ከየም ዞኖች የህብረት ስራ አመራሮች እና የሮዝመሪ አምራች አ/አደሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ አብዱልሀፊዝ መሀመድ

More Stories
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል