የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በወረዳው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ማድረጉን በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ግብርና፣ አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሣሁን ዳዒሞ ገልጸዋል።
በበልግና በምኸር ወቅቶች ለመትከል ከታቀደው 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞች በበልግ ተከላ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለው መጠናቀቁን ተከትሎ በምኸር ወቅት ተከላ የተቀረውን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል አቶ ካሣሁን ።
በወረዳው በበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በፍራፍሬ ችግኞች ላይ ትኩረት መደረጉን ያነሱት ኃላፊው በቀጣይም ዘርፈ-ብዙ ጥቅም ባላቸው ችግኞች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ኃላፊው አብራርተዋል ።
በአመያ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ 41 የችግኝ ጣቢያዎች መኖራቸውን በመጠቆም በነዚህ ሁሉም ጣቢያዎች ችግኞቹን ለተከላ ዝግጁ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል ።
ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞችም በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ የጽድቀት መጠናቸውም ከ 90 በ መቶ በላይ ስለመሆኑም ነው አቶ ካሣሁን የተናገሩት ።
በወረዳው ከሚገኙ ግብርና ባለሙያዎች መካከልም አቶ ሙሉዓለም ወዳጄ እና አቶ ዘውዴ ሾጋሞ በበኩላቸው ለመርሃ-ግብሩ በችግኝ ጣቢያዎቻቸው ችግኞችንና ጉድጓዶችን ለተከላ ዝግጁ የማድረግ ስራ መጠናቀቁን ገልፀዋል ።
በችግኝ ጣቢያዎች የስራ ዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ስለመሆኑ ተናግረዋል ።
ዘጋቢ ፡ ደረጀ ተፈራ ከዋካ ጣቢያ
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-