15ኛው ዙር ኾራ ኣታ ኾንሶ በዓል አስመልክቶ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) 15ኛው ዙር ኾራ ኣታ ኾንሶ በዓልን አስመልክቶ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።
የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበት 15ኛ ዓመትን በማስመልከት ነው ሲምፖዚየሙ እየተካሄደ ያለው።
የኮንሶ መልክዓ ምድር ሰኔ 20 ቀን 2003 ዓ.ም ለኢትዮጵያ 9 ነኛው የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወቃል።
በሲምፖዚየሙ የፌደራል የክልልና የዞኑ የስራ ኃላፊዎችና ምሁራን በተገኙበት ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።
በነገው ዕለት በካራት ከተማ በአደባባይ በዐሉ በድምቀት ይከበራል።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-