በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ አጀንዳ ለማሰባሰብ የተወካዮች ልየታ ላይ ያለመ መድረክ መካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 01/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ አጀንዳ ለማሰባሰብ የተወካዮች ምልመላ ላይ ያለመ መድረክ በሀዋሳ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ ከተለያዩ የህብረተሰብ አደረጃጀቶች የተውጣጡ አባላትት ተሳታፊ እየሆኑ ነው።
እራሳቸውን የሚገልፁበት ዋና መተዳደሪያ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ዕድሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የተገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ተፈናቃዮችን በአጀንዳ ቀረፃ ምክክር መድረክ ላይ ለማሳተፍ እየሰራ መሆኑን ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ