የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ፍትሃዊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ መስጠት ላይ ትኩረት አድርገው መስራት አለባቸው – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የጋራ ፎረም ተካሂዷል
በዚህ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ባስተላለፉት መልዕክት የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት የማህበረሰብ ለውጥ እንዲመጣ የራሳቸውን ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ጠቅሰው ይህንን ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ስራዎች በፍትሃዊነት ተደራሽ እንዲሆን ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡
ዕኩል እድል የተሰጣቸው አከባቢዎች የማስፈፀም አቅማቸውን አሟጦ በመጠቀም የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘጠና ዘጠኝ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች 8ቢሊየን ብር ካፒታል በማስመዝገብ በተለያዩ ዘርፎች የልማት ስራዎች አየሰሩ ይገኛሉ።
በፎረሙ በክልሉ ሁለንተናዊ ለውጥ ላይ የራሳቸውን አሻራ ላስቀመጡ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው የእውቅና ሰርተፊኬት አበርክተዋል።
ዘጋቢ :ሲሳይ ደበበ

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ