በወላይታ ሶዶ ከተማ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ
ዛሬ ከቀኑ ከ7:20 ኮድ (3)63419 ET የተሰኘ የፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪ ባደረሰው የትራፊክ አደጋ እስካሁን የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሶዶ ከተማ ፖሊሲ ዋና አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ገልፀዋል።
የአደጋው መንስኤ በጉዞ ላይ የነበረ ፍሳሽ ማስወገጃ መኪና ባገጠመው የቴክኒክ ችግር ሳቢያ ፍሬን አልታዘዝ ብሎት አደጋው መድረሱን ምክትል ኮማንደር ጠቁመዋል ።
በአደጋው ለህልፈት የተዳረጉት ሁለቱ በመንገድ ላይ የነበሩ የሌላ ተሸከርካሪ ረዳቶችና አንድ የሊስትሮ ባለሙያ
መሆኑን ታውቋል። ከባድ አደጋ የደረሰባቸው 3 ሰዎችም የህክምና እርዳታ እያገኙ ነው ፡፡
አደጋ አድራሹ ተሽከርካሪ መንገድ ዳር በነበሩ 6 ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት ማድረሱን ምክትል ኮማንድሩ ተናግረዋል ፡፡
ዘጋቢ ፡ በቀለች ጌቾ

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ