የወላይታ ዞን “ሁለንተናዊ የሴቶች ተሳትፎ ለጋራ ብልፅግና” በሚል ሀሳብ የተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዞናዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ

በመደረኩ የተገኙት የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል እንዳሉት፤ ሴቶች ለሀገር ግንባታ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካ እያበረከቱ ያለው አስተዋዕጾ የጎላ መሆኑን በመጠቆም ያለሴቶች ተሳትፎ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ አይቻልም።

በዞኑ በርካታ ሴቶች በአካባቢ የሚገኙ ፀጋዎችን በመጠቀም ኑሮአቸውን እንደለወጡም ተናግረዋል።

የወላይታ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል በበኩላቸው፤ እንደ ወላይታ ዞን ሴቶች በሁሉም ዘርፍ በመሳተፋቸው አበረታች ለውጦች እንዲመዘገቡ ማድረጉን ተናግረዋል።

ሴቶችን በውሳኔ ሰጪነት ለማብቃት ፓርቲዉ ከምንጊዜዉም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በርካታ ሴቶች በአረንጓዴ አሻራ፣ በህግ ማስከበር፣ በመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ፣ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ፣ ለትምህርት ቤቶች የመማሪያ መጽሀፍት ግዢ ዙርያ የሴቶች ተሳትፎ የጎላ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በመድረኩ የተገኙ ሴቶች በሰጡት ሀሳብ በአካባቢያቸው በመጣው ለውጥ በርካታ ሴቶች ወደ ዉሳኔ ሰጪነት በማደጋቸው የሚታይ ለውጥ በመምጣት ላይ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ዞን በርካታ ሴቶች ችሎታ እያላቸው እድል አጥተው የተቀመጡ ሴቶችን የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አሁንም ማብቃት እንዳለበት ተናግረዉ፤ በትምህርት ዕድሎች ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን