የ2017 ክልላዊ የበልግ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቤንች ሸኮ ዞን በሰሜን ቤንች ወረዳ ጠመንዣ ያዥ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ
በመርሀ ግበሩ የክልል የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አርሶ አደሮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው እንደገለፁት፤ በዘንድሮ የ2017 የበልግ አረንጓዴ አሻራ ከ399 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ይከተላሉ።
የአረንጓዴ አሻራው የማይበገር የአየር ንብረትን የሚቋቋም እንደሆነ የገለፁት አቶ ማስረሻ፤ መትከል ብቻ ሳይሆን የመንከባከቡ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን፤ በዞኑ ዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዞኑ ከ81 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከልም ተናግረዋል።
የሰሜን ቤንች ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ ጋይድ በበኩላቸው፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁመው እየተተከሉ ያሉትን በመንከባከብ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባም ገልፀዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ እንደገለፁት፤ በዞኑ ሰሜን ቤንች ወረዳ የ2017 ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ይፋዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የዞን፣ የወረዳና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ ተሳትፈዋል።
በመርሀ ግበሩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አርሶ አደሮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን

                
                                        
                                        
                                        
                                        
More Stories
በኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ግንባታ እና ተያያዥ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የጠቅላላ ተቋራጮች እና የአገልግሎት ተቋማት ትጋትና ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማህበራዊ ጫናዎችን ለመከላከል የኢኮኖሚ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላላት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለፀ
ትምህርት ቤቶች የዉስጥ ገቢያቸዉን በማሳደግ የግብዓት ችግሮችን በመቅረፍ ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢን መፍጠር እንዳለባቸዉ ተገለፀ