በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዱራሜ ክላስተር የግብርና ሴክተር ባለሙያዎች “የመሐሉ ዘመን” በሚል ርዕስ ወቅታዊና ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄዱ
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር የስልጠናና የውይይት ሰነዱን ለሴክተሩ ባለሙያዎች እንዳብራሩት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ የረጂም ጊዜ የፖለቲካ ታሪክ ያላትና በስኬትም በውድቀትም ያለፈችና የፀናች ሀገር ናት።
አቶ ኡስማን እንዳሉት፤ እየገጠሙን ያሉ ፈተናዎችን ወደ ዕድል እንዲሁም ዕድሉን ወደ ውጤት መቀየር ያስፈልጋል።
ባለፉት ዓመታት በተመዘገቡት ድሎች ሳንረካ በቀጣይም ሌሎች ስኬቶችን ማስመዝገብ ይጠበቅብናልም ብለዋል።
የግብርና ሴክተር የተለየ ተልዕኮ የሰነቀ መሆኑን ተገንዝበን ለሀገራዊ ስኬት በተሰማራንበት በሁሉም መስኮች መትጋት ግድ ይላል በማለት ገልፀዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዱራሜ ክላስተር የግብርና ሴክተር ባለሙያዎች የመሐሉ ዘመን በሚል ርዕስ በተካሄደው ወቅታዊና ሀገራዊ ውይይት “የመሐሉ ዘመን” ምንነት፣ ፍይዳና ፈተናዎችን በውል ለመረዳት የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ታደሰ
More Stories
በክልሉ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራ አሳረፉ
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው
በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።