በክልሉ የሻይ ተክል ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ

በክልሉ የሻይ ተክል ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሸ ዋጌሾ(ዶ/ር) የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ቦጊንዳ የሻይ ችግኝ ጣቢያን ጎብኝቷል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የሻይ ተክል ስራ በክልሉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፤ በወረዳው ቦጊንዳ ቀበሌ እየተዘጋጀ ያለው የዚሁ አንዱ ማሣያ ነው ብለዋል፡፡

በወረዳው የቦጊንዳ ቀበሌ የሰብል ባለሙያ አቶ ማሙሽ ገብሬ፤ የሻይ ችግኝ ተከላ ከዚህ ቀደም በነበረው ጊዜ ያልተለመደ መሆኑን ገልጸዋል።

የቦጊንዳ የሻይ ችግኝ ጣቢያ ለ2018 ዓመተ ምህረት በወረዳው የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች የሚሰራጭ የሻይ ችግኝ የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

500 ሺህ የሻይ ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስከአሁን ባለው 180 ሺህ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)፣ በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ፣ በምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ ጫካ – ከቦንጋ ጣቢያችን