በሐመር ወረዳ ሲካሄድ የነበረው የህዝብ ለህዝብ እና የምሁራን ውይይት ተጠናቀቀ

በሐመር ወረዳ ሲካሄድ የነበረው የህዝብ ለህዝብ እና የምሁራን ውይይት ተጠናቀቀ

ሀዋሳ፡ ግንቦት 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ የተካሔደው የህዝብ ለህዝብ ውይይትና የምሁራን መድረክ ሰላም፣ ልማትና አንድነትን ለማጠናከር የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ተጠኗቋል።

የሐመር ወረዳ፣ በቱርሚና ዲመካ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ለህዝብ ውይይትና የአከባቢው ተወላጅ ምሁራን እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ያሰተፈ መድረክ፥ ሰላም ልማትና አንድነትን ለማጠናከር ያለመ ለመሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሐመር ወረዳ ዲመካ ከተማ ከንቲባ አቶ ወሌ አልማ፥ የህዝባችንን የጋራ አንድነት በማጠናከር የተደራጀና የተቀናጀ አቅም መገንባት አሰፈላጊ በመሆኑ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በተደረገው ጥረት በልማት ሥራዎች አመርቂ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልፀው፥ በዚህም በከተማው የኢንቨስተሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።

መዋቅራዊ አንድነትን በመጠበቅ ለሁሉም ህዝብ ሰላማዊና ለኑሮ ምቹ ማድረግ የወረዳው ምሁራንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሁሉ አቀፍ ድጋፍ በማድረግ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሐመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ጋርሾ እንደገለፁት ለህዝብ ሰላምና አብሮነት ለዘላቂ ልማትና ብልፅግና የምሁራን መድረክ ያለው አበርክቶ የጎላ መሆኑን ጠቁመው፥ ጥሪያቸውን አክብረው ለታደሙ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ባደጉና በበለፀጉ ሀገራት ለህዝብ የጋራ ተጠቃሚነት የምሁራን ድርሻና ሃሳብ አመንጭነት የላቀ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው፥ ይህም ተቀራርቦ መወያየትና በያዙት የጋራ ሃሳብ ላይ በቅንጅት መስራት በመቻላቸው መሆኑን አመላክተዋል።

ምሁራን ለሰላም ግንባታ፣ ለዘላቂ ልማትና ብልፅግና የሃሳብ ልዩነቶችን በመነጋገርና በመግባባት ለአካባቢያቸው ለውጥና ዕድገት ብሎም ሀገራዊ ለውጥን ለማስመዝገብ ምክረ ሃሳቦችን በማፍለቅ የማይተካ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል።

በወረዳው የሚከናወኑ መደበኛ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ባሻገር በአካባቢያችን የሚከናወኑ ተግባራትን ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ለማስቻል ሊስራ እንደሚገባ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

በወረዳው ያሉት ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመቀነስና ለመቆጣጠር ሙሁራን የበኩላቸውን ሚና ልወጡ እንደምገባ ተገልጿል።

ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከርና የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በቅርበት በመደገፍ በመነጋገርና በመረዳዳት መልካም ገፅታን ለመፍጠር አንድነት ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ የደቡብ ኦሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወሊ ሐይሌ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ ሰነድ ቀርቦ ሀሳብና አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን፥ ቀደም ሲል ለወረዳው በተለያዩ እርከኖች ያገለገሉና አሁንም በማገልገል ላይ ለሚገኙ ምሁራን የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ዘጋቢ፡ አርኝሮ አርሻል – ከጂንካ ጣቢያችን