በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የሠላም፣ የልማት እና አንድነት ምክክር ተካሄደ

በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የሠላም፣ የልማት እና አንድነት ምክክር ተካሄደ

ሀዋሳ፡ ግንቦት 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በገረሴ ዙሪያ ወረዳና ገረሴ ከተማ አስተዳደር ከአከባቢው ተወላጅ ምሁራንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር የሠላም፣ የልማት እና አንድነት ምክክር ተካሂዷል፡፡

የምክክር መድረኩ የአከባቢው ምሁራንና ተወላጆች በልማት ተግባራት ላይ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑ ተመላክቷ፡፡

በከተማው የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ጠበኩሉን ድርሻ ሊያበረክት እንደሚገባ የገለጹት የጋሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀኪሜ አየለ፥ ዓለማችን በፈጣንና ተለዋዋጭ ጊዜ ውስጥ በመሆኗ የማህበረሰባችንን አንድነትና ብልጽግና ማረጋግጥ እጅግ ወሳኝነት እንዳለው ገልፀዋል።

ለህዝቡ ዘላቂ ልማት እጅግ ወሳኝነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ አንድነትን አጠናክረን ዕድሎችን መጠቀም ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የአከባቢን ሠላምን ማጽናትና የልማቱን ሥራ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመው፥ ለልማቱ በቁጭት የምንሰራበትና የበኩላችንን ድርሻ በአግባቡ መወጣትና ያለንን ሀብት መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ አከባቢው በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሀብቶች የበለፀገ በመሆኑ ይህንን አጣጥመን ተፎካካሪና ተወዳዳሪ ወረዳን ለመፍጠር ተቀናጅተን እንድንሰራ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው አቶ ወንድሙ ገዝሐኝ አንድነት ከግለሰብ ጀምሮ የሚመነጭና ለሠላም መጠናከር መሠረት እንደሆነ ጠቅሰው፥ እያንዳንዳችን ስለ ሠላም የምናስብ ከሆነ ሁሉም በቀላሉ ማከናወን እንደሚቻል አረጋግዋል።

በውይይቱ ቁም ነገር ይዘን ልማቱን ለማፋጠን የበኩላችን አስተዋፅኦ እናበርክት ብለዋል አቶ ወንድሙ።

በምክክር መድረኩ ላይ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳፊዎች በኩል ሀሳብና አስተያየት ቀርቦ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

ዘጋቢ፡ አበበ ዳባ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን