ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የምሑራኑ ውይይት ሰላም፣ ልማትና አንድነት ለማጠናከር ያለመ ለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ከተሳታፊ ምሑራን መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ከአመራሩ ጀምሮ ሁሉም የአከባቢው ነዋሪ አንድነትን የሚሽረሽሩ ጉዳዮችን አምርሮ በመታገል ከመጠላለፍ ፖለቲካ በመውጣት በጋራ ጥቅሞች በማተኮር የልማት ተጠቃሚነት ላይ በግልፅ በመተራረም ልንስራ ይገባል ብለዋል።
በተለይ በአርብቶ አደሩ አከባቢ የመንደር ማስባስብ፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የመስኖ እርሻና ሌሎችን ሥራዎች ጨምሮ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ወደ ተግባር ከመግባት አኳያ በቁርጠኝነት ለመስራትና ሚዛናዊ እይታ በማንጸባረቅ ሁሉም አንድነቱን ሊያጸና እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
ወረዳው እንዳለው እምቅ ፀጋ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከዞን ጀምሮ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ተደማጭ ለመሆን ከፖለቲካ ተሳትፎ ጀምሮ ሴቶችን ያሳተፈ ትግል ለማድረግና በልማት በመተጋገዝ መስራት ይገባል ተብሏል።
የሣላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ እና የወረዳው ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ባናና ጠብልጉ በጋራ እንደገለፁት በመልካም የተነሱ ሃሳቦችን በበጎ ጎን በመውስድ ድክመቶችን በማረም ሃሳብ በማዋጣት ከመገፋፋት፣ አጀንዳ ከመስጠት ወጥተን ለለውጥ በአንድነት መስራትና መታገል ያስፈልጋል ብለዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደስ ጋልጶክ በበኩላቸው ሁሉም ሰው ለሠላም ቅድምያ በመስጠት መገፋፋትን ትተን እንደ ምሁር በጋራ በመታገልና በመተጋገዝ በይቅርታ ለጋራ ዕድገት ልንስራ ይገባል።
በቀጣይ የምሁራን መማክርት ካውንስል ማቋቋም፣ የሰላም ኮሚቴ ካውንስል ማቋቋም እንዲሁም በወረዳው ጎበዝ ተማሪዎችን ደግፎ ማስተማር ቀጣይ በትኩረት አቅጣጫ መያዙ ተመላክቷል።
በውይይት መድረኩ ከዚህ በፊት ወረዳውን በከፍተኛ የሥራ ሃላፊነት ያገለገሉና ፌደራል በማገልገል ላይ የሚገኙ እንድሁም ለወረዳው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመድረኩ የፌዴራል፣ የክልል የሥራ ሃላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና የወረዳው ተወላጅ ሙሁራን የተሳተፉበት ሲሆን ባለ 12 ነጥብ የጋራ አቋም መግለጫ በማውጣት እርቅ በማድረግ በሃይማኖት አባቶች ምርቃትና ፀሎት ውይይቱ ተጠናቋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የጤና ተቋማት ግንባታ የህብረተሰቡን ፍላጎት የሚያሟሉና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሊሆኑ እንደሚገባ ተገለጸ
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው