በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄን ባህል በማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ስራን ማጎልበት ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አሳሰቡ
በጋርዱላ ዞን በዲራሼ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በየአካባቢው በመተግበር የተራቆቱ ተራሮችን ዳግም እንዲያገግሙ እየተደረገ ይገኛል።
የዚህ ተግባር አንድ አካል የሆነው በጋርዱላ ዞን በዲራሼ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
በተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትንጳኤ እንደተናገሩት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እድል ይሰጣል።
በሀገሪቱ ለባለፉት በርካታ አመታት እነዚህ መርሃ ግብሮች መከናወናቸውን ተከትሎ አለም ያረጋገጠውና የሚጨበጥ ለውጥ ተመዝግቧልም ብለዋል።
በጋርዱላ ዞን የዲራሼ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኪስሞ ኪታንቦ በበኩላቸው፤ በወረዳው በዚህ መርሃ ግብር 47 ሄክታር መሬትን በተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞች ለመሸፈን መቻሉንም ተናግረዋል።
የችግኝ ተከላው በወረዳው በከፍተኛ ሁኔታ የሚከሰተውን የመሬት ናዳና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል አይነተኛ አጋዥ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ ይህም ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት ከዚህ ቀደም ይደርስባቸው የነበረው ጎርፍና ናዳን በየጊዜው በሚካሄደው የችግኝ ተከላ ማስታገስ መቻሉን ተናግረዋል።
ዘጋቢ: በኃይሉ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ