ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
“ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለኢትዮጰያ መንሠራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ተገልጿል።
የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ዜና ማሞ በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፋ ሲሆን፤ ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ የብልጽግና ጉዞን ዕውን ማድረግ አለብን ብለዋል።
የማህበረበሰቡን ሁሉ አቀፍ የልማት ተሳታፊና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራው ተአማኒነት ያለው መረጃ ተደራሽ ማድረግ ስላለበት የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመሙላት የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስገንዝበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሸን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ሀላፊና የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ አዜብ ዘዉዱ፤ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት በማጠናከር ተአማኒነት ያለውን መረጃ በማድረስ በሀገራችን የተጀመሩ ለውጦችን ማስገንዘብ እንዲቻል የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ከመንግስት ጋር በመሆን የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎችን እንዲሁም ከነጠላ ትርክት በመውጣት የገዥ ትርክት ግንባታ ሚና ስራዎች ላይ ሚዲያ በበላይነት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተአማኒነት ያለውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ የተግባቦት ሚናውን ማጠናከር ይጠበቅበታል ነው ያሉት።
በመድረኩ የክልልና የዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊዎች የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎቻችን በመንግስትና በማህረሰቡ ዘንድ ተግባቦትን ለማጠናከር በምን መልኩ መተግበር እንዳለባቸውና ያሉ ማነቆዎችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዶችን አቅርበዋል።
በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ታድመዋል።
ዘጋቢ፡ ጽጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
መደበኛና በዘመቻ የሚሰጡ የክትባት አገልግሎቶች የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ መላው ህዝብ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ