በሣላማጎ ወረዳ ተወላጅ ምሁራን ሰላም፣ ልማትና አንድነትን ለማጠናከር ያለመ ውይይት በወረዳው ሃና ከተማ እየተካሄደ ነው

በሣላማጎ ወረዳ ተወላጅ ምሁራን ሰላም፣ ልማትና አንድነትን ለማጠናከር ያለመ ውይይት በወረዳው ሃና ከተማ እየተካሄደ ነው

መድረኩ በሀይማኖት አባቶች ፀሎትና ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡

የሣላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በሌሎችም ዘርፎች አበረታች የሚባሉ ውጤቶች ቢኖሩም በዚያው ልክ እንቅፋት የሆኑ የፀጥታ ጉዳይን ጨምሮ በየዘርፉ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመፍታት የጋራ አንድነት በመፍጠር የወረዳውን ሠላምና ልማት ለማረጋገጥ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መድረክ ነው ብለዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ታደስ ጋልጶክ፤ የወረዳው ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ለዘመናት ተዋደውና ተፈቃቅረው እየኖሩ መሆኑን አስታውሰው፤ ይህንን የዘመናት አብሮነትና ሠላም የአሁኑ ትውልድም እንዲያስቀጥል የጋራ መግባባት ማስፈለጉን አመላክተዋል።

አክለውም ወረዳው ከሌሎች አርብቶ አደር ወረዳዎች አንፃር ሲታይ ትልቅ ፀጋ ያለበት ወረዳ እንደመሆኑ ፀጋዎችን አውጥተን ለመጠቀም በተለይም በፀጥታና በሌሎችም ጉዳዮች አፅንኦት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

ምሁራኑ በዚህ የጋራ የሠላምና የአንድነት መድረክ በወንድማማችነትና እህትማማችነት በጋራ በመመካከር በቁጭት ለመፍታት የጋራ ሃሳብ የምንይዝበት ነው ብለዋል።

በምክክር መድረኩ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የወረዳ አመራሮችና ምሁራን እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች፣ የቀበሌ ሊቀ መናብርትና ሌሎችም የአካባቢው ነዋሪዎች እየተሳተፉበት ነው።

በውይይቱ የመነሻ ሰነድ እየቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎችም የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተው የጋራ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን